Beke Pre-Primary School
Announcement የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ተሠጠ

የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ተሠጠ

27th May, 2025

በቤኬ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ እድሚያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ተማሪዎች የኩፍኝ መከላከያ ክትባት ተሠጠ።

የትምህርት ቤቱ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተባባሪ የሆኑት ሚስ ቁምነገር ብዙአየሁ በዕለቱ ለተገኙ ወላጆች በጤና ባለሙያዎች አማካኝነት ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ የክትባት መስጠት መርሃግብሩ እንዲከናወን አድርገዋል።

በትምህርት ቤቱ የሚገኙ መምህራንና ሞግዚቶች የሚከተቡ ህፃናት ተማሪዎቹን በመለየት በማበረታታት የማረጋጋት ስራ ሰርተዋል።ህፃናት ተማሪዎችም ያለምንም ችግር ክትባታቸውን መውሰድ ችለዋል።

ግንቦት 19/2017

.

Copyright © All rights reserved.

Created with